መኑ የሐድገነ ፍቅሩ ለክርስቶስ nከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው?nክርስትና በተግባር በቤቱ ያጽናን አሜን!
About :
Contact:
Other Information
Categories:
Religious OrganizationWebsite:
http://Taketa.comFeatured Articles:
ከዕድሜ አንጻር ብዙ ጊዜ ራሳቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች ናቸው። ምክንያታቸውም በፆታ ጉዳይ በሚፈጠር ችግር፣ በአዕምሮ ጭንቀት፣ ከሱስ ጋር በተያያዙ ችግሮችና በሌሎች መሰል ነገሮች ነው። አዛውንቶች ግን ራሳቸውን ሲያጠፉ እምብዛም አይታይም። በመሐል መቀሌ ራሳቸውን የሰቀሉ አባት ሰሞኑን መመልከታችን እንደ ክፉ ምልክት የሚቆጠር ነው። ከዕድሜ ትምህርት ቤት ብዙ የተማሩ፣ መከራና ችግርን ደጋግመው የተሻገሩ፣ ለሕጻናትና ወጣቶች የጽናት ተምሳሌት የሆኑ፣ የመንደሩ አድባርና የማሕበረሰቡ ሽማግሌ የተሰኙ እንዲህ ያሉ አዛውንት ሲለዩ በእጅጉ ያሳዝናል። የኅብረተሰብ መሪ የሆኑ አዛውንት የተለዩት ራሳቸውን በአደባባይ ሰቅለው መሆኑ ደግሞ በሀገር ደረጃ አንገት የሚያስደፋ ነው። ኢትዮጵያ በወለጋ ዱር ውስጥ ካቀፈችው ልጅ ጋር በተገደለችው እናት እንደምትመሰል ሁሉ በመቀሌ በአደባባይ ራሳቸውን በሰቀሉ አባትም ትመሰላለች። እናም በሀገር ደረጃ ራስን ሁሉ ለህመም ልብንም ሁሉ ለድካም የዳረገን ብሔራዊ ችግር፣ ጭካኔና ክፋትን፣ ወንዜነትንና ዘውገኝነትን አስወግደን ፍቅርና መተሳሰብ ካላነገስን መጪው ጊዜ አስፈሪና አስከፊ ነው የሚሆነው። የአዛውንቱ ራስን ማጥፋት ያላራራው ልብና ምልክትነቱን ያልተረዳ ህሊና በራሱም ላይ የተቀጠረለትን መዓት ያልተገነዘበ ብቻ ነው።nnጌታ ሆይ እባክህ ዓይነ ልቡናችንን አብራልን..!
#እንኳን #አደረሳችሁnቅዱስ ገብርኤልn√ ሳጥናኤል በአመፀ ጊዜ መላእክትን በያለንበት እንቁም ብሎ ያረጋጋ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው።n√ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳናቸው ይህ መልአክ ነው።n√ ለሰው ሁሉ የምሥራች የሆነውን የጌታ መጸነስ ለድንግል ማርያም የአበሰረ መልአክ ነው።n√ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን የረዳቸው መልአክ ይህ ነው።n√ ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ሰላም፣ መጋቤ ሐዲስ ይባላል።nጸሎቱ ወበረከቱ ይኩን ምስለ ከልነ አሜን ፫
መንግስት ደግሞ ይሄንን ዶፒንግ ነው ብሎ ያስቀረው ይሆናል እኮ አያፍርም nእግዚአብሔር ሀይላችን ነው
ይሕ ደስታ ሩጫ ብቻ አይደለም ሌላ ብዙ ነገርም ያስተምረናል ባለ መስቀሎችም አልተቻሉም nእግዚአብሔር ይመስገን መስቀል ሀይላችን ነው
የባለፈው የእከ እከ ማለት 3(2) ልጅ ለወለደው መላካቸው ሲገርመን አሁንም ድጋሜ ሌላ ትኩሳት ክብር ለክሕነት ክብር ለጵጵስና nመምሕሩን በቅርብ የምታገኙት ምከሩት
በመስቀሉ ቀን በመስቀሉ አማትባ ወርቁን ቀምታ ድል ነሳያቸውnመስቀሉ ድል መንሻችን ነው።
ለክርስትና የተፈለ መስዕዋትነት አባታችን እግዚአብሔር ምሕረቱን ስለላከልዎት አኮቴት ለእርሱ ይድረስ nአባታችን ሆይ በጸሎትዎት አሁንም ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን ዘንድ አሳስቡልን nበረከታችሁም በእኛ ላይ ለዘላለም ጸንቶ ይኑርልን አሜን
የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪሕን አስብnመ.መክብብ ፲፪፣፩nየደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሰንበት ትምሕርት ቤት አባላት ግንቦት ፩ ፳፻፲፬ ዓ.ም nበቤቱ ያጽናን አሜንnለተጨማሪ መረጃ ፔጁን ላይክ እያደረጋችሁ